የ ክራንስተን ጥያቄ

የ ክራንስተን ጥያቄ ኣላማ ምንድነዉ፥

ይሄ የ ክራንስተን ጥያቄ የተቋቋመበት ኣላማ በ 24 ህዳር 2021 በለሊት ያጋጠመ በ ቻናል ላይ በትንሽ ጀልባ በትንሹ 27 ሰዎች ሂወታቸዉን ያጡበት ክስተት ለማየት ነዉ።

ገለልተኛ ከ መንግስት

ይሄ ገለልተኛ ነዉ፡ እናም ህጋዊ ስልጣን የሌለው ጥያቄ ሆኖ መደበኛዉ የሟቾች ምርመራ በሌለበት የሟቾችን ሁኔታ በተመለከተ ሙሉ ምርመራ ለማድረግ እንድያስችል የተነደፈ ነዉ። ይሄ ደሞ ራሱን ችሎ በ ሰር ሮስ ክራንስተን የሚመራ ነዉ።

ገለልተኛ ማለት ደሞ ምርመራው የመንግሥት አካል አይደለም፡ እና ደሞ በመንግስት ክፍል የሚመራ ኣይደለም።

ከእኛ ጋር ይገናኙ

እርሶ ከዛን በ 24 ህዳር 2021 ያጋጠመዉን ክስተት የተረፉ ወይ ደሞ የተጎጂዎችን ቤተሰብ ኖት፥ እንደዛ ከሆኑ፡ ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እኛን ማግኘት ከፈለጉ የኛ የአድራሻ ቅጽ (Link to contact form page) በመጠቀም ሊያገኙን ይችላሉ፡ ወይ ደሞ ቀጥለዉ ባሉት ኣማራጮችን በመጠቀም ሊሆን ይችላል፡

ኢሜይል: info@cranston.independent-inquiry.uk

ሜይል: ነጻ ፖስታ የ ክራንስተን ጥያቄ (FREEPOST The Cranston Inquiry)

እርሶን ለማግኘት በኢንግሊዝኛ ነዉ መሆን ያለበት፥

እኛን ለማናገር ከ እንግሊዝኛ ዉጪ በሌላ ቋንቋ እንዲሆንሎት ከፈለጉ፡ እባክዎ እኛን ያሳዉቁን እና የኛ የ ኣስተርጓሚ ኣገልግሎት በማቅረብ እርስዎን ማነጋገር እንችላለን።

በጥያቄው ሂደት ውስጥ መሳተፍ እፈልጋለሁ

እርስዎን ወክለዉ የሚሰሩ ጠበቃ ካሎት፡ እንዴት ሙሉ ተሳታፊ መሆን እንደሚቻል ጠበቃውን ያነጋግሩ ወይ ደሞ በዚ ኢሜይል በመላክ ጥያቄዎን ያቅርቡ info@cranston.independent-inquiry.uk.

ተጨማሪ መረጃ የት ማግኘት እችላለሁ፥

የበለጠ ለማወቅ ድህረ ገጻችንን መጎብኘት ይችላሉ። ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ የችሎት ቀናትን ያገኛሉ በድረ ገጻችን ላይ መረጃ እና ዜና የ ጥያቄዉን።

ጠቃሚ ድርጅቶች

እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ስለ ኢሚግሬሽን የሚመለከት ጉዳዮች ላይ መርዳት ወይም ምክር መስጠት አንችልም ይህ ደሞ ከምርመራው ወሰን ውጭ ስለሆነ ነዉ። በኢሚግሬሽን ሁኔታዎ ላይ እገዛ ከፈለጉ ወይም ስለ ጤናዎ የሚያሳስብዎት ከሆነ፡ እባክዎን ከታች ካሉት ድርጅቶች ውስጥ አንዱን ለማነጋገር አያመንቱ፡

Red Cross  
ለ ስደተኞች እና ጥገኝነት ፈላጊዎች ፈጣን የጤና እርዳታ ሊሰጥ ይችላል

Migrant Help – ኣሳይለም የእርዳታ መስመር 0808 8010 503
ለ ስደተኞች የምክር ኣገልግሎት እና እርዳታ ይሰጣል

Samaritans -. ወይም ስልክ ቁጥር. 116 123 ነጻ ነዉ
ለሚያስፈልጋቸዉ ሰዎች ነጻ የመስማት ኣገልግሎት